AddisClips - Ethiopian Entertainment Website
Welcome
Login
Powered by Daniel Tesfaye - Addis Clips

Most Popular Articles


 • የእጅ ጣታችን ርዝመት ስለ ማንነታችን ወይም ባህሪያችን ይገልፅ ይሆን?

  የእጅ ጣታችን ርዝመት ስለ ማንነታችን ወይም ባህሪያችን ይገልፅ ይሆን?

  ከዚህ በታች የምንመለከታቸው ምስሎችም የቀለበት ጣታችንና ሌባ ጣታችን ያላቸውን ርዝመት በማነፃፀር ባህሪያቶቻችን ለማወቅ ያስችላሉ ተብሏል።

  ምስሎቹ በጣታችን ርዝመት መሰረት A, B እና C በሚል የተቀመጡ ሲሆን፥ እርስዎም የጣትዎን ርዝመት በመመልከት በየትኛው እንደሚመደብ ከለዩ በኋላ ከዚህ በታች የተቀመጡት መግለጫዎች ከተጨባጭ ማንነትዎ ጋር ይስማማሉ አልያም ይቃረናሉ የሚለውን እንዲመለከቱ ጋብዘናል።

  1) "A"

  የቀለበት ጣት ከሌባ ጣት መብለጡን የሚያሳይ ነው - ምስል “A”።

  በዚህ ምድብ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች የቆንጆ ተክለሰውነት ባለቤት መሆናቸው ይነገራል።

  ሌሎች ሊያገኙት የሚጓጉለትን ነገር በቀላሉ ለማግኘት እንደሚችሉም ነው መረጃው የሚያመላክተው።

  በተጨማሪም እጅግ በጣም ተናዳጅና ለውሳኔ የፈጠኑና አደጋን ለመቀበል የማይፈሩ ናቸው ተብሏል።

  አብዛኞቹ ወታደሮች፣ ኢንጂነሮችና ቼዝ ተጫዋቾች ሲሆኑ የቃላት ድርደራ ጨዋታዎችን በመጫዎት የሚያህላቸው የለም።

  የቀለበት ጣታቸው ከሌባ ጣታቸው የሚረዝም ሰዎች አጭር የቀለበት ጣት ካላቸው ሰዎች ይልቅ የተሻለ ገቢ እንደሚያገኙም ሳይንቲስቶች አረጋግጠዋል።

  2) "B" በዚህ ምስል ላይ እንደምንመለከተው የቀለበት ጣት ከሌባ ጣት የሚያጥር ሲሆን፥ አጭር የቀለበት ጣት ያላቸው ሰዎች ከፍተኛ በራስ የመተማመን የተላበሱ መሆናቸው ይነገራል።

  ራስ ወዳድነትና ትእቢት ቢጤ የሚያጠቃቸው እንደሆኑም መረጃው ይገልፃል።

  ብቻቸውን መሆን የሚያስደስታቸው ሲሆን በእረፍት ስአታቸው መረበሽን አጥብቀው የሚጠሉ ናቸውም ተብሏል።

  በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ለመግባት ይፈራሉ የተባሉት ይህ አይነት የጣት አወቃቀር ያላቸው ሰዎች፥ በሌሎች ሰዎች እይታ ውስጥ መግባትን ግን የሚያደንቁና በጣም የሚፈልጉ ናቸው።

  3) "C" የቀለበት ጣትና የሌባ ጣት እኩል መሆናቸውን የሚያሳይ ነው።

  ሌባ ጣታቸውና የቀለበት ጣታቸው እኩል የሆኑ ሰዎች ሰላም ወዳድ እና ፀብና አለመረጋጋት ባለበት ቦታ ድርሽ ማለት የማያሹ ናቸው።

  እነዚህ ሰዎች ለነገሮች ትኩረት የሚሰጡና የተቀናጁ ሲሆኑ፥ ከበርካታ ሰዎች ጋር በቀላሉ የመግባባት ብቃት አላቸው።

  ለፍቅር ግንኙነትም ታማኝና ቅን ልቦና ያላቸው መሆኑ የሚነገር ሲሆን፥ አመለ ሸጋና ለፍቅር አጋራቸው እንክብካቤ የሚያበዙና የሚጠነቀቁ አይነት ሰዎች ናቸው።

  እስኪ እርሶም ይሞክሩትና ማንነትዎን ይገልፃል አይገልፅም የሚለውን ያረጋግጡ።

  ኤፍ.ቢ.ሲ

   

  Read more »
 • Teddy Afro - "Atse Tewodros II" Song Lyrics | May 7, 2017

  Teddy Afro - "Atse Tewodros II" Song Lyrics  

   

  የሰገደላት ውበቱ ፤ ያቺን የቃል መስታይት 

  ሞቶ ቀደማት ቴዎድሮስ ፤ ቆሞ ስቃዩዋን ላለማየት
  የወደቀላት ውበቱ ፤ ያቺን የቃል መስታይት
  ሞቶ ቀደማት ቴዎድሮስ ፤ ቆሞ ስቃዩዋን ላለማየት

  ደርሶ ባያስጥለው ፤ ገብርዬ ከስለት
  ጀግናው ተፈተነ ፤ በመቅደላ አቀበት
  ተዋከበና ፤ ተዋከበና
  ወዲህ ዞር ፤ ቢል ሰው የለምና
  ገብርዬ ሲወድቅ ፤ ቀኙ ዛለና
  አረሩን ስቦ ፤ ጠጣው ያ ጀግና
  ተዋከበና ፤ ተዋከበና
  ወዲህ ዞር ፤ ቢል ሰው የለምና

  የነደደ እሳት ፤ ክንዱን ተ'ርሶ
  ጨክኖ ካሣ ፤ ጋተና ኮሶ
  ሞተ 'ላንድ አገር ፤ አንድያ ራሱ
  ንቃ በመንፈስ ላንድነት ካሣ ተነሳ 
  አንተ የሞትክላት አገር ክብሯ ሳይረሳ

  ጎንደር ጎንደር የቴዎድሮስ አገር
  ያንዲት ኢትዮጵያ ፤ ዋልታና ማገር
  ነፍሱን የሰጣት ፤ ለካ ዓለም ንቆ
  አገር ሊያቆም ነው ቴዎድሮስ ወድቆ

  አምጡ ቆርጣችሁ ፤ ከሹሩባው ላይ 
  እንዳንለያይ ፤ ኪዳን እንሰር
  ነፍሱን የሰጣት ፤ ለካ ዓለም ንቆ
  አገር ሊያቆም ነው ፤ ቴዎድሮስ ወድቆ

  አረጀች እያሉ ሰዎቹ ሲያሙሽ
  ሙሽራ ነሽ ጎንደር ይሰፋል ልብስሽ
  ሳይገላገለው ህልሙን በሆድ ይዞ 
  ሳይገላገለው ሽሉን በሆድ ይዞ 
  የሚረዳው አጥቶ ብቻውን ተክዞ 
  ተክዞ ተክዞ
  ስንቱን በሆድ ይዞ
  የወገቡን እሳት ካፎቱ ላይ መዝዞ
  ጠጥቶላት ሞተ ክንዱን ተንተርሶ
  አያሳዝንም ወይ

  ካሣ ካሣ የቋራው አንበሣ
  ዳኘን ዳኘን አንድ ህልም አሳየን
  ዝግባ ሚያሳክለን አንድ ፍቅር አጥተን
  ዝግባ ሚያሳክለን አንድነትን አጥተን 
  ከፊት የነበርነው ከሰው ኋላ ቀርተን
  አናሳዝንም ወይ

  ጎንደርና ጎጃም ፤ ወሎና ትግራይ
  ኦሮሞና ተጉለት ሆነን አንድ ላይ
  ጉራጌና ሃረር ዶርዜ ወላይታ
  ቤኒሻንጉል ሶማሌ አፋር አሳይታ
  ግመሌን ላጠጣት እንደ አፋር ተጉዤ
  ግመሌን ላጠጣት ቀይ ባህር ተጉዤ
  አንድ ገመድ አጣሁ ልመልሳት ሄጄ
  'ያንዲት እናት ልጆች መሆናችን አውቀን
  ጎሳና ኃይማኖት ሳይነጣጥለን 
  ምን ይሳነን ነበር ብንተባበር
  አናሳዝንም ወይ

  ጎንደር ጎንደር የቴዎድሮስ አገር
  ያንዲት ኢትዮጵያ ፤ ዋልታና ማገር
  ነፍሱን የሰጣት ፤ ለካ ዓለም ንቆ
  አገር ሊያቆም ነው ፤ ቴዎድሮስ ወድቆ

  ቴዲ አፍሮ - አፄ ቴዎድሮስ ፪ኛ

   

  Read more »
 • ቴዲ አፍሮ በካቲት 26 2008 ሊቀርበው የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት ለሶስተኛ ጊዜ ጉዳዩ ይመለከተኛል ከሚለው የመንግስተ አካል ፈቃድ መከልከሉ በፌስቡክ ኦፊሴላዊ ገጹ ላይ አስታወቀ።

   

   

   

  ቴዲ አፍሮ በካቲት 26 2008 ሊቀርበው የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት ለሶስተኛ ጊዜ  ጉዳዩ ይመለከተኛል ከሚለው የመንግስተ አካል ፈቃድ መከልከሉ በፌስቡክ ኦፊሴላዊ ገጹ ላይ አስታወቀ።

  ቀደም ሲል በጳግሜ ወር 2007 የዘመን መለወጫ በዓል ዋዜማን ምክንያት በማረግ በላፍቶ ሞል ሊቀርብ የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት እና እንዲሁም በመስከረም 16 2008 ዓም የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ በተመሳሳይ ስፍራ (ላፍቶ ሞል) “በሰባ ደረጃ ወደ ፍቅር” በሚል ስያሜ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቆ ከሚመለከተው አካል ተገቢውን ፈቃድ ባለማግኘታችን ምክንያት በድጋሜ ፕሮግራሙ መሰረዙ የሚታወስ ነው።

  አሁን ደግሞ በቅርቡ በየካቲት 26 ቀን 2008 በጊዮን ሆቴል ሊካሄድ የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት በተመሳሳይ ሁኔታ ጉዳዩ ይመለከተኛል ከሚለው አካል ፈቃድ ለማግኘት በተደረገው ጥረት: በየዕለቱ ተለዋዋጭ በሆነ የውሳኔ አሰጣጥና እጅግ አድካሚ ከነበረ ተደጋጋሚ ውይይት በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ አለበቂ ምክንያት ዝግጅቱ እንዳይካድ መከልከሉን ለወዳጆቻችን እና ለአፍቃሪዎቻችን ስንገልፅ ከፍ ካለ ይቅርታ ጋር ነው።

  Read more »
RSS