AddisClips - Ethiopian Entertainment Website
Welcome
Login
Powered by Daniel Tesfaye - Addis Clips

Most Popular Articles


 • ETHIOPIA : Teddy Afro - "Mar ESKE TUWAF" Lyrics | ማር እስከ ጧፍ ፍቅር እስከ መቃብር

   

  Teddy Afro - "Mar ESKE TUWAF" Lyrics 

  ማር እስከ ጧፍ
  ፍቅር እስከ መቃብር

  የጸበል ዳር እንኮይ ወንዝ ያወዛት ቅጠል 
  ተሸፈና ዋርካ ከልሏት የዛፍ ጠል 
  የት ነበር ያረኩት ቀፎየን ስል ኖሬ 
  ንብ ተከትዬ ባይ ጎጃም ኑራ ማሬ (ጎጃም ኖራለች ለካ)

  ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ጓዴ 
  ተረሳሽ ወይ የሳት ዙሪያው ተረት በአንዴ
  ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ቀለም 
  እኔ እንዳንቺ ያጠናሁት ፊደል የለም

  ፍቅር የበዛበት፩ ዘልቆ ከማንኩሳ 
  መንናለች አሉኝ ብጫ ልብስ ለብሳ 
  ሸዋ ከሩፋኤል ስጠብቃት ኖሬ 
  ንቤ ገዳም ገብታ ጎጃም ኑራ ማሬ

  ሲኖዳ ዮሐንስ ያመት ወዜን ይዤ 
  ጋማ ሽጦ ካሳ፪ ሸኝቶኝ ከወንዜ 
  መጥቼ ከሸዋ ስጠብቃት ኖሬ 
  ለካ ገዳም ገብታ ጎጃም ኑራ ማሬ 
  “ሀ” ብለህ ተው ድገም ሲሉኝ ንስሀ አባቴ 
  “ዋ” ብየ ተማርኩኝ አይ አለመስማቴ 
  ቀለም ወርቄ፫ ቢሆን የቅርቤ ጓደኛ 
  ፍቅር ለያዘው ሰው ከልካይ የለው ዳኛ

  አሁን በማ ትኬ (ተክቼ) ይህ ልቤን ልካሰው 
  አንዴ በሷ ፍቅር የተረታሁኝ ሰው 
  የት እርቄስ ላገኝ ከፍቅሯ መሸሻ፬
  እሷ ሆኖ ለኔ የአለም መጨረሻ

  ማር ጧፍ ሁኔ /እንደ ትሁኔ/ 
  ማር ጧፍ ሁና 
  ማሬ ማሬ 4x
  ጎጃም ኑራ ማሬ 
  ማር ጧፍ ሆኖ ገባ መቅደስ 
  ነዶ ለሊት ጸሎት ሊያደርስ 
  ዲማ ጊዮርጊስ ወይ ማንኩሳ
  ያቺ ወንጌል፭ ብጫ ለብሳ 
  ከንግዲህማ ቆብ አስጥዬ 
  እንዳልወስዳት አባብዬ 
  ሰብልዬ ናት እማሆዬ 
  ሰብልዬ ናት እማሆዬ
  ሰብል አለም በቢጫው ቀለም 
  ሰብል የአዳም ገባሽ ወይ ገዳም 
  ወይ ገዳም ገባሽ ወይ ገዳም
  ኦሆ……

  የጸበል ዳር እንኮይ ወንዝ ያወዛት ቅጠል 
  ተሸፍና ዋርካ ከልሏት የዛፍ ጠል 
  የት ነበር ያረኩት ቀፎየን ስል ኖሬ 
  ንብ ተከትዬ ባይ ጎጃም ኑራ ማሬ

  ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ጓዴ 
  ተረሳሽ ወይ የሳት ዙሪያው ተረት በአንዴ
  ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ቀለም 
  እኔ እንዳንቺ ያጠናሁት ፊደል የለም

  ላሳደገኝ ደብር የሥለት ልጅ ሆኜ 
  ካሕን እንዴት ይፍታኝ ያንቺ እስረኛ ሆኜ 
  በጊዜ ተደፋ የቀለሙ ቀንዴ 
  የኔ ፊደል ማወቅ ካንቺ አዳነኝ እንዴ 
  ሳዋህድ ከኖርኩት ቅኔን ከደብተሬ 
  ተሽሎኝ ተገኘ ባለ አንዲሩ ገብሬ፮
  ለካ ሰው አይድንም በደገመው መጽሐፍ 
  እንደሰም አቅልጦ ፍቅር ካረገው ጧፍ 
  ለካ ሰው አይድንም በኦሪቱ ገድል 
  ወንጌል ይዞ መጥቶ ፍቅር ካረገ ድል

  ማር ሲገባ ገዳም ድንጋይ ተንተርሶ 
  ጧፉም እንደ መናኝ እዩት ቢጫ ለብሶ 
  ወንጌል መነኮሱ በልጅነታቸው 
  ማር እስከጧፍ ሆኖ አለም ቢነዳቸው
  አንቺ የፍቅር ጥጌ ውድነሽ በጣሙን፯
  መምጣቴ ነው በቃ እኔ አቃተኝ አሁን 
  አዲስ አለም፰ ሆነ ባንቺ ስለ ወጋየሁ፱ 
  እድሌ ሆነና ባጣሽ ተሰቃየው

  ማር ጧፍ ሁኔ 
  ማር ጧፍ ሁና 
  ማሬ ማሬ 4x
  ጎጃም ኑራ ማሬ 
  ማር ጧፍ ሆኖ ገባ መቅደስ 
  ነዶ ለሊት ጸሎት ሊያደርስ 
  ዲማ ጊዮርጊስ ወይ ማንኩሳ
  ያቺ ወንጌል ብጫ ለብሳ 
  ከንግዲህማ ቆብ አስጥዬ 
  እንዳልወስዳት አባብዬ 
  ሰብልዬ ናት እማሆዬ 
  ሰብልዬ ናት እማሆዬ
  ሰብል አለም በቢጫው ቀለም 
  ሰብል የአዳም ገባሽ ወይ ገዳም 
  ወይ ገዳም ገባሽ ወይ ገዳም
  ኦሆ…… 
  ዘንግ ይዛ ማር ዘንግ ይዛ

  ---------------------//--------------------

  ግጥም - ቴዎድሮስ ካሳሁን 
  ዜማ - ቴዎድሮስ ካሳሁን 
  ሙዚቃ ቅንብር - አቤል ጳውሎስ /ናደው/

  በዘፈኑ ግጥም ውስጥ የተሰመረባቸው ፱ ነጥቦች ደርቦ ከሚሄደው ትርጉማቸው ጀርባ የሚጠቀሱ የባህሪያት ስሞች መፅሀፉን ላላነበቡ ወገኖች ይረዳ ዘንድ የተሰጠ መጠነኛ ማብራሪያ
  1. የበዛባት፡- በዛብህ የሰብለወንጌል ፍቅረኛን
  2. ካሳ፡- ጉዱ ካሳ የሰብለወንጌል አጎትና የሰብለና የበዛብህ የፍቅር አጋርን
  3. ቀለምወርቄ፡- ግራጌታ ቀለመወርቅ የበዛብህ የቅርብ ወዳጅን
  4. መሸሻ፡- ፊት አውራሪ መሸሻ የሰብለወንጌል አባትን
  5. ወንጌል፡- ሰብለወንጌል የበዛብህ ፍቅረኛን
  6. ባለአንዲሩገብሬ፡- እረኛው ባለዋሽንት ባለአንዲሩገብሬ የካብትሽ ይመር ወዳጅን
  7. ውድነሽ በጣሙን፡- የበዛብህ እናት ውድነሽ በጣሙን
  8. አዲስዓለም ሆነ፡- የፍቅር እስከ መቃብር መፅሀፍ ደራሲ ክቡር ሀዲስ ዓለማየሁን
  9. ወጋየሁ፡- የመፅሀፉን ተራኪ ተዋናይ ወጋየሁ ንጋቱን
  ይገልፃል።

  ይህ ሙዚቃ መታሰቢያነቱ ለፍቅር እስከ መቃብር መፅሀፍ ደራሲ ለክቡር አቶ ሀዲስ አለማየሁ እና ለመጸሐፉ ተራኪ ለተዋናይ ወጋየሁ ንጋቱ ይሁንልኝ፡፡

  Read more »
 • ቴዲ አፍሮ በካቲት 26 2008 ሊቀርበው የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት ለሶስተኛ ጊዜ ጉዳዩ ይመለከተኛል ከሚለው የመንግስተ አካል ፈቃድ መከልከሉ በፌስቡክ ኦፊሴላዊ ገጹ ላይ አስታወቀ።

   

   

   

  ቴዲ አፍሮ በካቲት 26 2008 ሊቀርበው የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት ለሶስተኛ ጊዜ  ጉዳዩ ይመለከተኛል ከሚለው የመንግስተ አካል ፈቃድ መከልከሉ በፌስቡክ ኦፊሴላዊ ገጹ ላይ አስታወቀ።

  ቀደም ሲል በጳግሜ ወር 2007 የዘመን መለወጫ በዓል ዋዜማን ምክንያት በማረግ በላፍቶ ሞል ሊቀርብ የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት እና እንዲሁም በመስከረም 16 2008 ዓም የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ በተመሳሳይ ስፍራ (ላፍቶ ሞል) “በሰባ ደረጃ ወደ ፍቅር” በሚል ስያሜ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቆ ከሚመለከተው አካል ተገቢውን ፈቃድ ባለማግኘታችን ምክንያት በድጋሜ ፕሮግራሙ መሰረዙ የሚታወስ ነው።

  አሁን ደግሞ በቅርቡ በየካቲት 26 ቀን 2008 በጊዮን ሆቴል ሊካሄድ የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት በተመሳሳይ ሁኔታ ጉዳዩ ይመለከተኛል ከሚለው አካል ፈቃድ ለማግኘት በተደረገው ጥረት: በየዕለቱ ተለዋዋጭ በሆነ የውሳኔ አሰጣጥና እጅግ አድካሚ ከነበረ ተደጋጋሚ ውይይት በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ አለበቂ ምክንያት ዝግጅቱ እንዳይካድ መከልከሉን ለወዳጆቻችን እና ለአፍቃሪዎቻችን ስንገልፅ ከፍ ካለ ይቅርታ ጋር ነው።

  Read more »
 • Ethiopian Airlines flight diverted from Addis Ababa to St. John’s

  Flight landed at 4 p.m. NT following medical emergency

  By Garrett Barry, CBC News
  January 26,2017

  Ethiopian Airlines, seen here in a file photo, diverted one of its planes to St. John’s on Wednesday. (Tiksa Negeri/Reuters) (CBC)

   

  A medical emergency aboard a flight bound for Ethiopia’s capital city diverted a plane to St. John’s on Wednesday.

  Ethiopian Airlines Flight 501 landed in St. John’s at about 4 p.m NT, according to Erika Kelland, a spokesperson at the St. John’s International Airport.

  Kelland said there was a medical emergency on board, but had no other information about the incident or how long the plane would remain in St. John’s.

  The plane left Washington, D.C. at 11:30 NT and was set for a flight of about 13 hours to Addis Ababa.

  Source : CBC News

  Read more »
 • ግዙፉ የመረጃ ማፈላለጊያ ድረ ገጽ ጎግል ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው እለት የአማርኛ ትርጉም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

   

   

  ግዙፉ የመረጃ ማፈላለጊያ ድረ ገጽ ጎግል ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው እለት የአማርኛ ትርጉም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ። ከዚህ በፈት ከነበሩት ቋንቋዎች  አማሪኛ ጨምሮ 13 አዲስ ቋንቋዎች አካቶዋል። በዚህ አገልግሎት አማሪኛ ጽሁፍ የጎግል ጹሁፍ ማስገቢ ውስጥ በማስገባት ወደ ሚፈልጉት ቋንቋ እንዲተረጉምሎት ማድረግ ይቻላሉ።

  ሲፈልጉ ደግሞ በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉት መረጃዎች ኮፒ ፔስት በማድረግ ወድ አማሪኛ ቋንቋ እንዲተረጉምልን ማድረግ ይቻላል። በዚህ አገልግሎትም እንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ አረብኛ፣ ስፓኒሽ፣ ጣሊያንኛ፣ ቻይንኛ፣ ራሺያኛ፣ ፖርቹጊስ፣ ስዋሂሊ፣ ሶማልኛ፣ አፍሪካናስ እና ቱርኪሽን ጨምሮ ወደ 104 ቋንቋዎች ይተረጉምልናል።

  አገልግሎቱን ለማግኘትም https://translate.google.com/#en/am/ethiopia/ በሚል አድራሻ ስንገባ ለጽሁፍ ማስገቢያ ክፍት ቦታ ይመጣልናል። እንግሊዘኛ ውይም አማሪኛ በመጻፈ አገልግሎቱ ማግኝት እንችላለን።

  ለምሳሌ የሚከተለው የአማሪኛ ጹሁፍ ወደ እንግሊዘኛ እንዲተረጉምልን እናድረግ።  ውጠቱን ስእሉ ላይ ይመልከቱ ወይም ጹሁፉ ኮፒ ፔስት በማድረግ ውጤቱ ማየት ይችላሉ።

  ጎግል ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው እለት የአማርኛ ትርጉም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ። 

   

  ፍጽም ትክክለኛ ትረጉ እናዳይጠብቁ ምክኒያቱ አዲስና ሊሻሻል የሚችል ነው።  እናም ማነኛውም ስው እንዲሻሻል አስተዋጾ ማበረከት ይችላል።

   

   

   

   

  Read more »
RSS