AddisClips - Ethiopian Entertainment Website
Welcome
Login
Powered by Daniel Tesfaye - Addis Clips

Entertainment


 • ETHIOPIA : Teddy Afro - "Mar ESKE TUWAF" Lyrics | ማር እስከ ጧፍ ፍቅር እስከ መቃብር

   

  Teddy Afro - "Mar ESKE TUWAF" Lyrics 

  ማር እስከ ጧፍ
  ፍቅር እስከ መቃብር

  የጸበል ዳር እንኮይ ወንዝ ያወዛት ቅጠል 
  ተሸፈና ዋርካ ከልሏት የዛፍ ጠል 
  የት ነበር ያረኩት ቀፎየን ስል ኖሬ 
  ንብ ተከትዬ ባይ ጎጃም ኑራ ማሬ (ጎጃም ኖራለች ለካ)

  ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ጓዴ 
  ተረሳሽ ወይ የሳት ዙሪያው ተረት በአንዴ
  ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ቀለም 
  እኔ እንዳንቺ ያጠናሁት ፊደል የለም

  ፍቅር የበዛበት፩ ዘልቆ ከማንኩሳ 
  መንናለች አሉኝ ብጫ ልብስ ለብሳ 
  ሸዋ ከሩፋኤል ስጠብቃት ኖሬ 
  ንቤ ገዳም ገብታ ጎጃም ኑራ ማሬ

  ሲኖዳ ዮሐንስ ያመት ወዜን ይዤ 
  ጋማ ሽጦ ካሳ፪ ሸኝቶኝ ከወንዜ 
  መጥቼ ከሸዋ ስጠብቃት ኖሬ 
  ለካ ገዳም ገብታ ጎጃም ኑራ ማሬ 
  “ሀ” ብለህ ተው ድገም ሲሉኝ ንስሀ አባቴ 
  “ዋ” ብየ ተማርኩኝ አይ አለመስማቴ 
  ቀለም ወርቄ፫ ቢሆን የቅርቤ ጓደኛ 
  ፍቅር ለያዘው ሰው ከልካይ የለው ዳኛ

  አሁን በማ ትኬ (ተክቼ) ይህ ልቤን ልካሰው 
  አንዴ በሷ ፍቅር የተረታሁኝ ሰው 
  የት እርቄስ ላገኝ ከፍቅሯ መሸሻ፬
  እሷ ሆኖ ለኔ የአለም መጨረሻ

  ማር ጧፍ ሁኔ /እንደ ትሁኔ/ 
  ማር ጧፍ ሁና 
  ማሬ ማሬ 4x
  ጎጃም ኑራ ማሬ 
  ማር ጧፍ ሆኖ ገባ መቅደስ 
  ነዶ ለሊት ጸሎት ሊያደርስ 
  ዲማ ጊዮርጊስ ወይ ማንኩሳ
  ያቺ ወንጌል፭ ብጫ ለብሳ 
  ከንግዲህማ ቆብ አስጥዬ 
  እንዳልወስዳት አባብዬ 
  ሰብልዬ ናት እማሆዬ 
  ሰብልዬ ናት እማሆዬ
  ሰብል አለም በቢጫው ቀለም 
  ሰብል የአዳም ገባሽ ወይ ገዳም 
  ወይ ገዳም ገባሽ ወይ ገዳም
  ኦሆ……

  የጸበል ዳር እንኮይ ወንዝ ያወዛት ቅጠል 
  ተሸፍና ዋርካ ከልሏት የዛፍ ጠል 
  የት ነበር ያረኩት ቀፎየን ስል ኖሬ 
  ንብ ተከትዬ ባይ ጎጃም ኑራ ማሬ

  ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ጓዴ 
  ተረሳሽ ወይ የሳት ዙሪያው ተረት በአንዴ
  ብራናዬ አንቺ የልጅነቴ ቀለም 
  እኔ እንዳንቺ ያጠናሁት ፊደል የለም

  ላሳደገኝ ደብር የሥለት ልጅ ሆኜ 
  ካሕን እንዴት ይፍታኝ ያንቺ እስረኛ ሆኜ 
  በጊዜ ተደፋ የቀለሙ ቀንዴ 
  የኔ ፊደል ማወቅ ካንቺ አዳነኝ እንዴ 
  ሳዋህድ ከኖርኩት ቅኔን ከደብተሬ 
  ተሽሎኝ ተገኘ ባለ አንዲሩ ገብሬ፮
  ለካ ሰው አይድንም በደገመው መጽሐፍ 
  እንደሰም አቅልጦ ፍቅር ካረገው ጧፍ 
  ለካ ሰው አይድንም በኦሪቱ ገድል 
  ወንጌል ይዞ መጥቶ ፍቅር ካረገ ድል

  ማር ሲገባ ገዳም ድንጋይ ተንተርሶ 
  ጧፉም እንደ መናኝ እዩት ቢጫ ለብሶ 
  ወንጌል መነኮሱ በልጅነታቸው 
  ማር እስከጧፍ ሆኖ አለም ቢነዳቸው
  አንቺ የፍቅር ጥጌ ውድነሽ በጣሙን፯
  መምጣቴ ነው በቃ እኔ አቃተኝ አሁን 
  አዲስ አለም፰ ሆነ ባንቺ ስለ ወጋየሁ፱ 
  እድሌ ሆነና ባጣሽ ተሰቃየው

  ማር ጧፍ ሁኔ 
  ማር ጧፍ ሁና 
  ማሬ ማሬ 4x
  ጎጃም ኑራ ማሬ 
  ማር ጧፍ ሆኖ ገባ መቅደስ 
  ነዶ ለሊት ጸሎት ሊያደርስ 
  ዲማ ጊዮርጊስ ወይ ማንኩሳ
  ያቺ ወንጌል ብጫ ለብሳ 
  ከንግዲህማ ቆብ አስጥዬ 
  እንዳልወስዳት አባብዬ 
  ሰብልዬ ናት እማሆዬ 
  ሰብልዬ ናት እማሆዬ
  ሰብል አለም በቢጫው ቀለም 
  ሰብል የአዳም ገባሽ ወይ ገዳም 
  ወይ ገዳም ገባሽ ወይ ገዳም
  ኦሆ…… 
  ዘንግ ይዛ ማር ዘንግ ይዛ

  ---------------------//--------------------

  ግጥም - ቴዎድሮስ ካሳሁን 
  ዜማ - ቴዎድሮስ ካሳሁን 
  ሙዚቃ ቅንብር - አቤል ጳውሎስ /ናደው/

  በዘፈኑ ግጥም ውስጥ የተሰመረባቸው ፱ ነጥቦች ደርቦ ከሚሄደው ትርጉማቸው ጀርባ የሚጠቀሱ የባህሪያት ስሞች መፅሀፉን ላላነበቡ ወገኖች ይረዳ ዘንድ የተሰጠ መጠነኛ ማብራሪያ
  1. የበዛባት፡- በዛብህ የሰብለወንጌል ፍቅረኛን
  2. ካሳ፡- ጉዱ ካሳ የሰብለወንጌል አጎትና የሰብለና የበዛብህ የፍቅር አጋርን
  3. ቀለምወርቄ፡- ግራጌታ ቀለመወርቅ የበዛብህ የቅርብ ወዳጅን
  4. መሸሻ፡- ፊት አውራሪ መሸሻ የሰብለወንጌል አባትን
  5. ወንጌል፡- ሰብለወንጌል የበዛብህ ፍቅረኛን
  6. ባለአንዲሩገብሬ፡- እረኛው ባለዋሽንት ባለአንዲሩገብሬ የካብትሽ ይመር ወዳጅን
  7. ውድነሽ በጣሙን፡- የበዛብህ እናት ውድነሽ በጣሙን
  8. አዲስዓለም ሆነ፡- የፍቅር እስከ መቃብር መፅሀፍ ደራሲ ክቡር ሀዲስ ዓለማየሁን
  9. ወጋየሁ፡- የመፅሀፉን ተራኪ ተዋናይ ወጋየሁ ንጋቱን
  ይገልፃል።

  ይህ ሙዚቃ መታሰቢያነቱ ለፍቅር እስከ መቃብር መፅሀፍ ደራሲ ለክቡር አቶ ሀዲስ አለማየሁ እና ለመጸሐፉ ተራኪ ለተዋናይ ወጋየሁ ንጋቱ ይሁንልኝ፡፡

  Read more »
 • Teddy Afro - "Atse Tewodros II" Song Lyrics | May 7, 2017

  Teddy Afro - "Atse Tewodros II" Song Lyrics  

   

  የሰገደላት ውበቱ ፤ ያቺን የቃል መስታይት 

  ሞቶ ቀደማት ቴዎድሮስ ፤ ቆሞ ስቃዩዋን ላለማየት
  የወደቀላት ውበቱ ፤ ያቺን የቃል መስታይት
  ሞቶ ቀደማት ቴዎድሮስ ፤ ቆሞ ስቃዩዋን ላለማየት

  ደርሶ ባያስጥለው ፤ ገብርዬ ከስለት
  ጀግናው ተፈተነ ፤ በመቅደላ አቀበት
  ተዋከበና ፤ ተዋከበና
  ወዲህ ዞር ፤ ቢል ሰው የለምና
  ገብርዬ ሲወድቅ ፤ ቀኙ ዛለና
  አረሩን ስቦ ፤ ጠጣው ያ ጀግና
  ተዋከበና ፤ ተዋከበና
  ወዲህ ዞር ፤ ቢል ሰው የለምና

  የነደደ እሳት ፤ ክንዱን ተ'ርሶ
  ጨክኖ ካሣ ፤ ጋተና ኮሶ
  ሞተ 'ላንድ አገር ፤ አንድያ ራሱ
  ንቃ በመንፈስ ላንድነት ካሣ ተነሳ 
  አንተ የሞትክላት አገር ክብሯ ሳይረሳ

  ጎንደር ጎንደር የቴዎድሮስ አገር
  ያንዲት ኢትዮጵያ ፤ ዋልታና ማገር
  ነፍሱን የሰጣት ፤ ለካ ዓለም ንቆ
  አገር ሊያቆም ነው ቴዎድሮስ ወድቆ

  አምጡ ቆርጣችሁ ፤ ከሹሩባው ላይ 
  እንዳንለያይ ፤ ኪዳን እንሰር
  ነፍሱን የሰጣት ፤ ለካ ዓለም ንቆ
  አገር ሊያቆም ነው ፤ ቴዎድሮስ ወድቆ

  አረጀች እያሉ ሰዎቹ ሲያሙሽ
  ሙሽራ ነሽ ጎንደር ይሰፋል ልብስሽ
  ሳይገላገለው ህልሙን በሆድ ይዞ 
  ሳይገላገለው ሽሉን በሆድ ይዞ 
  የሚረዳው አጥቶ ብቻውን ተክዞ 
  ተክዞ ተክዞ
  ስንቱን በሆድ ይዞ
  የወገቡን እሳት ካፎቱ ላይ መዝዞ
  ጠጥቶላት ሞተ ክንዱን ተንተርሶ
  አያሳዝንም ወይ

  ካሣ ካሣ የቋራው አንበሣ
  ዳኘን ዳኘን አንድ ህልም አሳየን
  ዝግባ ሚያሳክለን አንድ ፍቅር አጥተን
  ዝግባ ሚያሳክለን አንድነትን አጥተን 
  ከፊት የነበርነው ከሰው ኋላ ቀርተን
  አናሳዝንም ወይ

  ጎንደርና ጎጃም ፤ ወሎና ትግራይ
  ኦሮሞና ተጉለት ሆነን አንድ ላይ
  ጉራጌና ሃረር ዶርዜ ወላይታ
  ቤኒሻንጉል ሶማሌ አፋር አሳይታ
  ግመሌን ላጠጣት እንደ አፋር ተጉዤ
  ግመሌን ላጠጣት ቀይ ባህር ተጉዤ
  አንድ ገመድ አጣሁ ልመልሳት ሄጄ
  'ያንዲት እናት ልጆች መሆናችን አውቀን
  ጎሳና ኃይማኖት ሳይነጣጥለን 
  ምን ይሳነን ነበር ብንተባበር
  አናሳዝንም ወይ

  ጎንደር ጎንደር የቴዎድሮስ አገር
  ያንዲት ኢትዮጵያ ፤ ዋልታና ማገር
  ነፍሱን የሰጣት ፤ ለካ ዓለም ንቆ
  አገር ሊያቆም ነው ፤ ቴዎድሮስ ወድቆ

  ቴዲ አፍሮ - አፄ ቴዎድሮስ ፪ኛ

   

  Read more »
RSS