AddisClips - Ethiopian Entertainment Website
Welcome
Login
Powered by Daniel Tesfaye - Addis Clips

News


 • ኢትዮጲያና ኤርትራ ወደ ሙሉ ጦርነት መግባታቸውን የተለያዩ የመንግስት ደጋፍ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው፡፡

   

  ኢትዮጲያና ኤርትራ ወደ ሙሉ ጦርነት መግባታቸውን የተለያዩ የመንግስት ደጋፍ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው፡፡     

  ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በእገላ/ፆረና ግንባር - በገና - በለሳ ወንዝ አከባቢዎች በከባድ መሳሪያ የታገዝ ጦርነት እያካሄዱ መሆኑ  Hornaffairs  እና አውራባ ታይምስ ዝግበዊታል፡፡   ከሁለቱም ሀገራት በኩል መረጋምንም የተስጠ ማረጋገጫ የለም።

   

  ornaffairsRead more 

  Read more »
 • ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም የኢትዮጵያን በሱማሌ መወረር በማስመልከት ያደረጉት የእናት አገር ጥሪ ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለ ቀበሮ ይሻላል!

   

  ሶማሊያ እንደ ሃገር ነፃነቷን ባገኘች ማግስት ካራመደቻቸው ሃሳቦች መካከል አንዱ ማንኛውም ሶማልኛ ቇንቇ የሚናገር ህዝብ ወደ ታላቇ ሶማሊያ መካተት አለበት የሚል ነበር። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሶማሊኛ ተናጋሪ ህዝቦች የሚኖሩበትን የምስራቁን የኢትዮጵያ ክፍል በ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. ወረረች። ይህንን ወረራ በማስመልከት በወቅቱ የሃገሪቱ መሪ የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም ወደ ጦር ግንባር ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን የሚያመለክት ወታደራዊ ልብስ ለብሰው በሚያዚያ ፬ ቀን ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. በተሌቪዝን የሚከተለውን ጥሪ አስተላለፉ።
  ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም።
  "... ታፍራ እና ተከብራ የኖረችው ኢትዮጵያ ተደፍራለች። ባሁኑ ሰዓት የአብዮታዊት እናት ሃገራችን ዳር ድንበርና የማይገሰሰው አንድነታችን በውጭ ኃይል እየተደፈረ ነው። በአብዮታችንና በአንድነታችን በጠቅላላው በብሄራዊ ህልውናችን ላይ የሚደረገው ወረራና ድፍረት እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ደርሷል... ለብዙ ሺህ ዘመናት አስከብሮን የኖረው አኩሪ ታሪካችን በዚህ አብዮታዊ አዲስ ትውልድ ጊዜ መጉደፍ የለበትም። አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያዊት! የኢትዮጵያ ህዝብ! ክብርህንና ነፃነትህን ለመድፈር፣ አገርህን ለመቁረስ... የተጀመረውን ጣልቃ ገብነትና ወረራ ከመለዮ ለባሹ ጋር ተሰልፈህ ለመደምሰስ የምትዘጋጅበት ጊዜ አሁን ነው። ተነስ! ታጠቅ! ተዋጋ! እናሸንፋለን!!"
  ምንጭ:
  "እኛና አብዮቱ"
  ፍቅረስላሴ ወግደረስ

  Read more »
 • ቴዎድሮስ ካሳሁን ለምን "ቴዲ አፍሮ" ተባለ?

   

  ቴዲ የ፲፪ (12)ኛ ክፍል ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ሰፊ ጊዜ ሥለነበረው ከመቸውም በተለየ ሁኔታ በዚያን ጊዜ ነበር በእግር በፈረስ ሥለሙዚቃ መጋለብ እና መሮጥ የጀመረው። ፲፱፻፺፩ (1991) አመተ ምህረት አካባቢ ከ ያሬድ ሙዚቃ ቤት ተመርቀው የወጡ ባለሙያዎች ላስታስ የተባለ የሙዚቃ ባንድ አቇቁመው ነበር:: በዚያን ጊዜ ቴዲ የራሱ የሆነ ባንድ እንዲኖረው ይፈልግ ሥለነበር ከሙያ ጉዋደኞቹ ጋር መመሆን በወቅቱ የነበሩትን ጥሩ ጥሩ የሙዚቃ መሳሪያዎች በመግዛት ላስታስ ከተባለው የሙዚቃ ባንድ ጋር አብሮ ለመሠራት ያላቸዉን ፍላጎት ለባንዱ አባላት ይገልፃሉ:: የባንዱ አባላትም በደስታ ይቀበሉዋቸዋል:: ብዙም ሳይቆዩ የባንዱ ስያሜ ከላስታስ ወደ አፍሮ ሳዉንድ ቀየሩት::
  ቴዲ አፍሮ
  ባንዱንም በበላይነት በመቆጣጠር እና በመምራት ቴዲ ትልቅ ድርሻና ሃላፊነት ነበረው:: መሳሪያ ተጫዋቾቹ እንደሚሉት ከሆነ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን ፣ ሽዋንዳኝ ሃይሉ እና ግሩም መዝሙር የአፍሮ ሳውንድ ባለቤቶች ተብለው የሚጠቀሱ ሲሆን "ቴዲ ግን እንደ ባንዱ ባለቤት ብቻ ሣይሆን እንደ ቅርብ ጏደኛችን ነበር የምናየው" ይሉታል። እንግዲህ በዚሕ ጊዜ ነበር ቴዎድሮስ ካሣሁን የሚለው ስሙ በቴዲ አፍሮ ተተክቶ ዋነኛ መጠሪያ ስሙ ለመሆን የበቃው።
  ምንጭ:
  የቴዲ አፍሮ የታላቅነት ምስጢር ፣ አቤል ዘበነ ሀ/ወልድ

  Read more »
 • ሀገር ማለት ልጄ፣ ሀገር ማለት፣ እንዳይመስልሽ የተወለድሽበት ቦታ ፣ የተወለድሽበት አፈር፤ - በዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ

   

   

  ሀገር ማለት ልጄ፣ ሀገር ማለት፣
  እንዳይመስልሽ የተወለድሽበት ቦታ ፣ የተወለድሽበት አፈር፤
  እትብትሽ የተቀበረበት ፣ ቀድመሽ የተነፈሽው አየር፤
  ብቻ እንዳይመስልሽ።
  ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤
  አገር ውስብስብ ነው ውሉ።

  ሀገር ማለት ልጄ ፣
  ሀገር ማለት ምስል ነው ፣በህሊና የምታኖሪው፤
  ከማማ መህጸን ከወጣሽበት ቀን ጀምሮ ፤
  በጠባሽው ጡት፣ ወይም ጡጦ ፣
  በዳህሽበት ደጃፍ፣ በወደቅሽበት ፈፋ፤
  በተማርሽበት ትምህርት ቤት፣
  በተሻገርሽው ዥረት ፤
  በተሳልሽበት ታቦት ፣ወይ በተማፀንሽው ከራማ ፤
  በእውቀትሽና በህይወትሽ፣
  በእውነትሽና በስሜትሽ ፣
  የምትቀበይው ምስል ነው ፣ በህሊናሽ የምታኖሪው፤
  ስትወጅ ሰንደቅ ታደርጊው፡፡
  ቢያስጠላሽ የማትቀይሪው።

  ሀገር ማለት የኔ ልጅ ፣
  ሀገር ማለት ቋንቋ ነው በአንደበት አይናገሩት፤
  በጆሮ አያዳምጡት፤
  አማርኛ ኦሮሞኛ ፣ አፋርኛ ቅማንተኛ፤
  ጉራግኛ ወይ ትግርኛ፣ ብለው የማይፈርጁት ።

  የኔ ልጅ፣
  አማራውና አፋሩ፣ ኦሮሞው ሲዳማው ፣ ጉራጌኛሽን ባይሰማ፤
  ያለገባው እንዳይመስልሽ ፣ ሀዘን ደስታሽን ያልተጋራ።
  የየልቦናችንን ሀቅ፣ ፍንትው አድርጎ እያሳየ፤
  ህዝቦችን ከሰንደቃቸው፣ አስተሳስሮ ያቆየ፡፡
  ሀገር ቋንቋ ነው ልጄ፣ የሁለንተናሽ መስታወት፤
  ሲከፋሽ ትሽሽጊበት ፣ ሲደላሽ ትኳኳየዪበት ።

  የኔ ልጅ ፣
  አያት ቅም አያትሽ ፣ሰላም ሲሆን ከወልቂጤ አድማስ ማዶ ሸቅጦ፣
  ሲያቀና ወረቱን፤
  ለእኔና ለአንቺ መኖሪያ፣ ሲያቀና ቀዬና ቤቱን፤
  ሀገር ጠላት ሲደፍራትም፣ ጦሩን ሰብቆ እየፎከረ፤
  ከኦሮሞው ከትግሬው፣ ከአፋሩ ከወላይታው፣ . . . ከሁሉም የጦቢያ ልጆች ፣
  አጥንቱን እየማገረ፤
  ሀገር ይሉት መግባቢያ ፣ሰንደቅ ይሉት መለያ ፣ ሲያቆይልሽ፤
  በጉራግኛ ማትገልጭው፣ በጎጥ የማትገድቢው፣ ስንት አለ ታሪክ መሰለሽ!

  እና የእኔ ልጅ፣
  ለዚህ ነው ሀገር ይሉት ቋንቋ፣ ላንቺ የሚያስፈልግሽ፤
  ከወልቂጤ አድማስ ማዶ፣ ለተሳሰረ ታሪክሽ፤
  ከወልቂጤ አድማስ ማዶ ፣ ለተወጠነው እድገትሽ።
  እና ልብ በይ ልጄ ! ሀገር ማለት ቋንቋ ነው፣ ባንደበት አይናገሩት፤
  በጆሮ አያዳምጡት።

  ከሁሉም በላይ ልጄ ፣
  ተፈጥሮ ከቸረው በረከት ፣ የላቡን ፍሬ የሚበላ፤
  ሀገር ማለት ወገን ነው፣ የእኔ የምትይው ከለላ።
  ትመኪበት ጥሪት፣ ትደምቂበት ብርሃንሽ፤
  የሰብዕናሽ ግማሽ ውል ፣ወገን ነው ማሕተምሽ፡፡
  ዜጋው ነው ልጄ ሀገርሽ።

  መሬትማ የእኔ ልጅ፣
  በእምነትሽና እውቀትሽ፣ ከልለሽ ካላበጀሽው፤
  ለእድገትሽ ውጥን ካልሆነ ፣ለተስፋሽ ካልተመገብሽው፤
  መሬትማ ባዳ ነው፣ ላለማው የሚለማ፤
  ለተስማማው የሚስማማ።
  ዥረቱም ግድ የለውም ፣ ቦይ ለማሰለት ይፈሳል
  ተራራውም ደንቆሮ ነው ፣ ለቦረቦረው ይበሳል።
  መሬቱ አደለም የኔ ልጅ፣ እድርተኛው ነው ሃገርሽ፤
  ስትቸገሪ ታድጎ፣ ስትታመሚ አስታሞ፣ ስትሞቺ አፈር ሚያለብስሽ።
  በእጅሽ ያለ ብሩህ ጽጌ ፣ ሰው ነው ልጄ ሀገርሽ፤
  ወገን ነው ልጄ ሀገርሽ።

  እና የኔ ልጅ፣
  ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤
  ሀገር ውስብስብ ነው ውሉ።

  Read more »
 • The world's happiest - and least happy - countries

  Denmark regains title of 'world's happiest country'

  Denmark has been declared the planet’s most contented country, pipping Switzerland, Iceland, Norway and Finland to top spot in the annual World Happiness Report.

   At the other end of the table,  Burundi was rated the least happy country, with a score of just 2.905, followed by Syria, Togo, Afghanistan and Benin. The lowest European country in the rankings was Bulgaria, at 129th, while Greece and Portugal also performed badly, sitting 99th and 94th, respectively. The United States rose two places to 13th.

  Read More 

   

  Read more »
RSS